Fana: At a Speed of Life!

ከመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት በኋላ ለህዳሴ ግድብ የሚደረገው የገንዘብና የፖለቲካ ድጋፍ መጨመሩ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የታላቁየኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት መካሄድን ተከትሎ ለግድቡ የሚደረገው የገንዘብና ፖለቲካዊ ድጋፍ መጨመሩን የግድቡ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ገለፀ።

ከመሰረተ ድንጋይ መቀመጥ ማግስት የጀመረው ድጋፍ ለ9 ዓመታት መቀጠሉን በታለቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባባሪያ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት የህዝብ ግንኙነት ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሀይሉ አብርሃም ይናገራሉ።

የህዝቡ የእስካሁን ድጋፍን 13 ቢሊየን ብር የተሻገር ሲሆን፥ በፋይናስ ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪ ፖለቲካዊ ድጋፍ ግደቡ ዛሬ የደረሰበት ደረጃ እንዲገኝ ማድረጉንም አንስተዋል።

ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የሚያደርጉት ድጋፍ በየትኛውም አስገዳጅ ሁኔታ ውስጥ ቢሆኑም ድጋፋቸውን ከማድረግ የሚያግዳቸው ነገር እንደሌለም አሳይተዋል ብለዋል።

ትውልድ ኢትዮጵያውኑ በግል የሚያድረጉት እንቅሰቃሴ ተምሳሌት እየሆነ በመምጣቱ በመካከለኛው ምስራቅ የኢትዮጵያን ትክክለኛ አቋም የሚያሳውቁና የሚከራከሩ ከ200 በላይ በአረብኛ ቋንቋ የሚስሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊን እንዲኖሩ አስችሏል።

መንግስትም የሀገርን ጥቅም ለማስጠበቅ ባለው ቁርጠኝነት ከውስጥና ከውጭ የሚደርሱበትን ግፊቶች ጥበብ በተሞላበት አመራር እንዲጓዝ አድርጓል።

የለውጥ አመራሩ በግድቡ ግንባታ ሂደት ላይ ያሳየው ቁርጠኝነትም የመጀመሪያው ዙር የውሃ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ እንዲያጠናቅ ማስቻሉን ነው ዳይሬክተሩ የሚናገሩት።

የውሃ ሙሌቱን ተከትሎም በአጭር ጊዜ ውስጥ ህዝቡ ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓልም ነው ያሉት።

በፋይናስ ከተደረገው ድጋፍ በተጨማሪ ድምፁን በአንድ ቀን ለዓለም በማሰማት ያሳየው ፖለቲካዊ ድጋፍም ከፍተኛ ደረጃ ተጎናጽፏል።

በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እስካሁን 46 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር በጥሬ ገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸውንም በበጽህፈት ቤቱ የዳያስፖራ ተሳትፎ፣ ፐብሊክ ዲፕሎማሲና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሄኖክ አለማየሁ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያውንና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ በፋይናስ እያደረጉ ካለው ድጋፍ በተጨማሪ በቡድንና በተናጥል በሙያቸው በድርድር ሂደት ምክረ ሀሳብ በማቅረብ እየሰጡ ያለው ድጋፍም ከፍተኛ ነው ብለዋል።

በዚህም የግብፅ የተዛቡ ትርክቶችን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማስረዳት በመካከለኛው ምስራቅ፤ በአሜሪካ እና አውሮፓ የኢትዮጵያን ፍትህዊ ተጠቃሚነት መርህን እያስተዋወቁ መሆኑንም ገልፀዋል።

በበላይ ተስፋዬ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.