Fana: At a Speed of Life!

በቻምፒየንስ ሊጉ አር ቢ ሌፕዚግ የግማሽ ፍጻሜተፋላሚ መሆኑን አረጋገጠ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት ምሽት የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ተካሄዷል፡፡

አር ቢ ሌፕዚግ እና አትሌቲኮ ማድሪድን ባገናኘው ጨዋታ የጀርመኑ ክለብ የግማሽ ፍጻሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

በፖርቹጋል ሊዝበን በተደረገው በዚህ ጨዋታ አር ቢ ሌፕዚግ ጨዋታውን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ኦልሞ እና አዳምስ ለአርቢ ሌፕዚግ የድል ጎሎቹን ሲያስቆጥሩ ሲኩዬራ ለአትሌቲኮ ማድሪድ የማስተዛዘኛዋን ጎል አስቆጥሯል፡፡

ይህን ተከትሎም የጀርመኑ ክለብ ከፈረንሳዩ ፒ ኤስ ጂ በግማሽ ፍጻሜው ይገናኛል፡፡

ፒ ኤስ ጂ ከትናንት በስቲያ የጣሊያኑን አታላንታን በተመሳሳይ 2 ለ 1 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

ባርሴሎና ከባየርን ሙኒክ እንዲሁም ማንቼስተር ሲቲ ከሊዮን ሌሎች የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ናቸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.