Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ፖሊስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ  ህግን የተላለፉ አካላትን 50 ሚሊየን ብር መቅጣቱን ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 11 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ ክልል የፖሊስ ሀይል የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር  የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ  ህግ የተላለፉ አካላትን 50 ሚሊየን ብር መቅጣቱን ገለጸ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከልና ትራፊክ ምክትል ዘርፍ ሀላፊ ረዳት ኮሚሽነር ሙሉ ሁነኛው÷  የፀጥታ ሀይሉ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ህግን በማስከበር በኩል ጠንካራ  አደረጃጀትና ስምሪት ፈጥሮ በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች እየሰራ እንደሚገኝ  ተናግረዋል።

በዚህም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ህግ የተላለፉ 7 ሺህ 912 የተለያዩ ተሽከርካሪዎች 15 ሚሊየን 940 ሺህ 818 ብር መቀጣታቸውንም ነው የተናገሩት።

የትራፊክ ህግና ደንብን በተደጋጋሚ የተላለፉ 8 ሺህ 46 አሽከርካሪዎች  በፍርድ ቤት ተከሠው 72 አሽከርካሪዎችን ከአንድ ወር እስከ አንድ አመት በሚደርስ እስራት መቀጣታቸውንም ገልጸዋል።

7 ሺህ 928  አሽከርካሪዎች ደግሞ 12 ሚሊየን  491 ሺህ 338 ብር መቀጣታቸውን እና 53ቱ አሽከርካሪዎች ደግሞ በቀጠሮ ላይ እንደሚገኙም  ነው ረዳት ኮሚሽነሩ ያስረዱት።

በተመሣሣይ ሁኔታ የአስቸኳይ  ጊዜ አዋጁን ክልከላ የጣሱ 7 ሺህ 578 ተጠርጣሪዎችን ለህግ እንዲቀርቡ  በማድረግ 337 ተከሳሾች በእስራት እንዲቀጡ መደረጉም ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈም 6 ሺህ 417 ተከሳሾች  14 ሚሊየን 244 ሺህ 135 ብር መቀጣታቸውንም ጠቁመዋል።

በተጨማሪም ልዩ ልዩ ደንብ የተላለፉ 25 ሺህ 51 አሽከርካሪዎች ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ በማድረግ  ከ7 ሚሊየን 435 ሺህ ብር በላይ መቀጣታቸውም ተገልጿል ፡፡

አሁን ላይ በተለይም ህዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው የተለያዩ ስፍራዎች መዘናጋት እየተስተዋለ በመሆኑ የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ን እንዲያስተምሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በናትናኤል ጥጋቡ

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.