Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ በዓለም እጅግ ከፍተኛ ሊሆን ይችላል የተባለ የሙቀት መጠን መመዝገቡ ተነገረ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 11 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ በዓለም እጅግ ከፍተኛ ሊሆን ይችላል የተባለ የሙቀት መጠን መመዝገቡ ተነገረ፡፡

የሙቀት መጠኑ 54 ነጥብ 4 ዲግሪ ሴሊሺየስ ሲሆን ካሊፎርኒያ በሚገኘው ዴዝ ቫሊ ፓርክ የተመዘገበ ነው ተብሏል፡፡

ከፍተኛ ነው የተባለው የሙቀት መጠን በሃገሪቱ ብሄራዊ አየር ትንበያ አገልግሎት እየተጣራ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በአሜሪካ ምዕራባዊ ዳርቻዎች በዚህ ሳምንት በተለይም ሰኞ እና ማክሰኞ ከፍተኛ የሆነ የሙቀት መጠን እንደሚመዘገብም የአየር ትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ባለፈው ቅዳሜ በከፍተኛ ሙቀት ሳቢያ በካሊፎርኒያ በአንድ የሃይል ማመንጫ ማዕከል ላይ በደረሰ ብልሽት ሳቢያ ለሁለት ቀናት የሃይል አቅርቦት መቋረጡ ነው የተነገረው።

ከዚህ ባለፈም በግዛቲቱ ደረቃማ በሆኑ አካባቢዎች የእሳት ነበልባል መታየቱንም የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በዚሁ ስፍራ 54 ዲግሪ ሴሊሺየስ የሙቀት መጠን በፈረንጆቹ 2013 እንደተመዘገበ ይነገራል፤ ይህም እስካሁን ከፍተኛው ሆኖ ቆይቷል፡፡

አንዳንድ “የተአማኒነት” ችግር አለባቸው የተባሉ መረጃዎች ደግሞ በፈረንጆቹ 1931 በቱኒዚያ 55 ዲግሪ ሴሊሺየስ መጠን ያለው የሙቀት መጠን መመዝገቡን ያመላክታሉ፡፡

ምንጭ፣ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.