Fana: At a Speed of Life!

የከተማዋን እድገት በሚፈለገው መንገድ ለማፋጠን የገቢና ወጪ ስርዓቱን ሚዛናዊነት መጠበቅ ይገባል – ኢ/ር ታከለ ኡማ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የከተማዋን እድገት በሚፈለገው መንገድ ለማፋጠን የገቢና ወጪ ስርዓቱን ሚዛናዊነት መጠበቅ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገለፁ፡፡
 
በአዲስ አበባ ከተማ በገቢ አሰባሰብ እና በኢኮኖሚው ዘርፍ የሚታየውን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችና መፍትሄዎችን በተመለከተ ከዘርፉ አመራሮች ጋር ውይይት ተደርጓል።
 
ኢንጂነር ታከለ የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱ በቴክኖሎጂ ሊዘምን እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
 
ከግብር እና ቀረጥ አሰባሰቡ ጋር የሚስተዋሉ ችግሮች በአፋጣኝ ሊፈቱ ይገባልም ነው ያሉት።
 
ህዝብ በሚበዛባቸው ተቋማት ላይ የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋ እና ተደራሽ ከማድረግ ባለፈ ብልሹ አሰራሮችን እንዲታረሙ ከተማ አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት ይሰራልም ብለዋል።
 
በተጨማሪም በየጊዜው የሚሰጡ ስልጠናዎች ችግር ፈቺ ሆነው ወደ ተግባር ሊቀየሩና ለውጥ ሊያመጡ እንደሚገባ መናገራቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
#FBC
 
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.