Fana: At a Speed of Life!

ተጨማሪ 1 ሺህ 460 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ16 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 11 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ19 ሺህ 747 ሺህ ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 1 ሺህ 460 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡

ሚኒስትሯ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ 165 ሰዎች ባለፉት 24 ሰአታት ከቫይረሱ ማገገማቸውን አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም የ16 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ይህን ተከትሎም በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 544 ደርሷል፡፡

አሁን ላይም 213 ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ ይገኛሉም ተብሏል፡፡

በአጠቃላይ እስካሁን በኢትዮጵያ ለ629 ሺህ 210 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 31 ሺህ 336 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ከዚህ ውስጥ 18 ሺህ 266 ሰዎች ቫይረሱ ያለባቸው ሲሆን 12 ሺህ 524 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.