Fana: At a Speed of Life!

ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ድጋፍ ለማድረግ 333 የስልክ መልዕክት የገቢ ማሰባሰቢያ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 12፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ድጋፍ ለማድረግ 333 የስልክ መልዕክት የገቢ ማሰባሰቢያ ይፋ ሆነ።

ለገበታ ለሀገር ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ለኢትዮጵያ ብልጽግና አሻራቸውን የሚያኖሩበት እንዲሆን የተዘጋጅ መርሃ ግብር መሆኑ ተጠቁሟል።

በዚህም መሰረት የጎርጎራ፣ ወንጪ እና ኮይሻ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶች ለመደገፍ ኢትዮጵያ በ333 አጭር ቁጥር የፈለጉትን የብር መጠን መላክ እንደሚችሉ ነው የተገለፀው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገበታ ለሃገር ባስጀመሩበት ወቅት ገንዘብ፣ እውቀት እና ጉልበት በማሰባሰብ ተፈጥሮን ሳናውክ ለዜጎችም ለውጭ ቱሪስቶችም የምትመች ኢትዮጵያን እንፈጥራለን ማለታቸው የሚታወስ ነው።

በተመሳሳይ በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የሚሳተፉበትን መንገድ እንደሚያሳውቅ ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.