Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ ያለፉ መልካም ተሞክሮዎችን በማጠናከር ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግና አሳታፊ ዴሞክራሲ እንደሚገነባ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ዝቅተኛ አመራሮች በብልጽግና ፓርቲ ዙሪያ ውይይት እያካሄዱ ነው፡፡

በዚህ ወቅት የብልፅግና ፓርቲ ያለፉ መልካም ተሞክሮዎችን በማጠናከር ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ እና አሳታፊ ዴሞክራሲ መገንባት የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል።

ውይይቱ በውህደቱ አስፈላጊነት ፣ ሂደት እና በፓርቲው ህገ ደንብ ዙሪያ ያተኮረ ነው፡፡

በዚህ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከክፍለ ከተማው አስር ወረዳዎች የተውጣጡ 1 ሺህ 500 ዝቅተኛ አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

በትግዕስት አብርሃም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.