Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ከ2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ሆኖ የቀረበለትን የክልሉ መንግስት የ2013 በጀት አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ከ2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ሆኖ የቀረበለትን የክልሉ መንግስት የ2013 በጀትን በዛሬው እለት አፀደቀ።

የሐረሪ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ዛሬም ቀጥሎ ሲካሄድ ውሏል።

ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎውም  2 ቢሊየን 509 ሚሊየን 505 ሺህ 021 ብር በሆኖ በክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የቀረበለትን የ2013 የክልሉ መንግስት በጀት ተመልክቷል።

ምክር ቤቱም በ2013 የክልሉ መንግስት በጀት ላይ ከተወያየ በኋላ ማፅደቁን የሐረሪ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

በ2013 በጀት ዓመት በተለይም የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ የመመለስ፣ የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ስራና ኮሮና ቫይረስ የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባር ቅድሚያ እንዲሚሰጥ በጉባዔው ላይ ተነስቷል።

በትላንትናው እለት የተጀመረው የክልሉ ምክር ቤት ስብሰባ በነገው እለት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.