Fana: At a Speed of Life!

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ሰራተኞች ለገበታ ለሀገር የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለገሱ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 13 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ሰራተኞች ለገበታ ለሀገር የአንድ ወር ደመወዛቸውን መለገሳቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።
 

ገበታ ለሀገር የሁላችንም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ  ለዚህ ብሔራዊ ዕቅድ እንዲውል እራሳቸውን ጨምሮ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ሰራተኞች የአንድ ወር ደመወዛቸው ለግሰዋል ።

እያንዳንዱ የጽህፈት ቤቱ ባልደረባ አሻራውን እየተወ መሆኑን በመግለፅ እናንተም እንዲሁ እንደምታደርጉ ተስፋ አደርጋለሁ ነው ያሉት።
 
በዛሬው ዕለት በገበታ ለሀገር ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉትን የገንዘብ መጠን እንዲያዋጡ የተዘጋጀውን የባንክ ሂሳብም ይፋ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡
 
በዚህም የ10 ሚሊየን እና የ5 ሚሊየን ብር ገቢ ለማድረግ እንዲሁም ከሀገር ውስጥ ማንኛውም መጠን ያለውን ገንዘብ አስተዋጽዖ ለማድረግ የባንክ ሂሳብ ቁጥር፦ 1000339911267 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ እንዲጠቀሙ ተጠይቋል።
 
እንዲሁም ከሃገር ውጭ ለሚገኙ ወገኖች በ0100101300591 የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መጠቀም ይችላሉ፡፡
በተጨማሪም መላው ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉትን ያህል የገንዘብ መጠን ለማዋጣት ወደ 333 አጭር የጽሑፍ መልዕክት በመላክ አሻራቸውን እንዲያሳርፉም ጥሪ ቀርቧል።።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.