Fana: At a Speed of Life!

ታላቁ የህዳሴ ግድብ የነጻነት አርማችን ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 14 ፣ 2012 (ኤፍ. ቢ.ሲ) የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ታላቁ የህዳሴ ግድብ የነጻነት አርማችን ሲሉ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የቦርድ አባላትና የፕሮጀክቱ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ሪፖርት በቀረበላቸው ወቅት ነው።

በሪፖርቱ ላይ በዚህ ዓመት በተሰራ ጠንካራ ስራ ፕሮጀክቱ በታቀደለት ጊዜ ማስኬድ ከመቻሉም በላይ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ አፈጻጸምም 75 በመቶ መድረሱ ተመላክቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያን ለመለወጥ ከኢትዮጵያውያን የተደመረ ጥረት ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌለ የታየበትም ነው ብለዋል ።

ታላቁ የህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ በቅኝ ያልተገዛች ሀገር ብቻ ሳትሆን በአፍሪካ ነጻ ሆና መቀጠሏን ያረጋገጥንበት ፕሮጀክታችንም ሲሉ ተናግረዋል ።

አክለውም ከዛሬ ጀምሮ የሁሉም ኢትዮጵያዊ በቀጣይ ዓመት ስራዎችን ማሳካት ላይ ማተኮር ይገባዋልም ብለዋል።

አያይዘውም የህዳሴው ግድብ ግንባታ ላይ እንቅፋት የሚፈጥር የትኛውም ግለሰብም ሆነ ሀይል በኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ላይ እንደቆመ ይቆጠራል ብለዋል።

በአላዛር ታደለ

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.