Fana: At a Speed of Life!

ም/ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች በመዲናዋ በትኩረት በሚሰሩ ጉዳዮች ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 14 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በቀጣይ ሁለት ወራት በመዲናዋ በትኩረት በሚሰሩ ጉዳዮች ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያዩ።

ምክትል ከንቲባዋ በውይይቱ ላይም በቀጣይ ትኩረት ተደርጎ የሚሰራባቸው ተግባራት ዙሪያ ገለፃ አድርገዋል።

በዚህም በቀጣይ ሁለት ወራት የኮሮና ቫይረስን መከላከል፣ የሁሉም ሴክተሮችን አገልግሎት አሰጣጥ ቀልፋነት እና ፍትሃዊነትን ማሻሻል ላይ በተለይም በመሬት ምዝገባና አርሶ አደሮች መሬት ዞታ ማረጋገጫ ላይ በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት።

እንዲሁም የገቢ አሰባሰብ፣ የስራ እድል ፈጠራ፣ የተጀመሩ የፕሮጀክት ግንባታዎችን ማፋጠን እና ሰላም እና ፀጥታ ማስከበር ላይ እንደሚሰራ ነው ምክትል ከንቲባዋ ወይዘሮ አዳነች የተናገሩት።

በአሁን ሰዓትም በመርሃ ግብሩ ተሳታፊ የሆኑ ተቋማት ሪፖርት እያቀረቡ ሲሆን፥ በመጨረሻም ምክትል ከንቲባዋ የስራ መመሪያም ሰጥተዋል።

በለይኩን ዓለም

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.