Fana: At a Speed of Life!

የዴሞክራቱ ዕጩ ጆ ባይደን የዶናልድ ትራምፕን የጨለማ ዘመን እንዲያበቃ እሰራለሁ አሉ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የዴሞክራቶች እጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይዳን የ2020 የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን ካሸነፉ የፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተዳደር የጨለማ ዘመን እንዲያበቃ እሰራለሁ ሲሉ ቃል ገብተዋል።

ጆ ባይዳን ላለፉት አራት ዓመታት አሜሪካን ያስተዳደሯት ዶናልድ ትራምፕ ለረጅም ጊዜ አሜሪካን በጨለማ ውስጥ እንድትቆይ አድርገዋል በማለት ወቅሰዋቸዋል።

የቀድሞው የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ÷ ትራምፕ ከፍ ያለ ፍርሃት፣ ቁጣ እና መከፋፈልን ፈጥረዋልም ብለዋል።

በትውልድ ከተማቸው ዊልሚግተን ባደረጉት ንግግር የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት እንድሆን እምነታችሁ ከሆነ በጎ የሆነ ነገር እንጅ ጎጂውን ተግባር አልፈፅምም ነው ያሉት።

የ77 ዓመቱ እጩ ፕሬዚዳንት እየተካሄደ በሚገኘው የጠቅላላ ምርጫ ዘመቻ በተሰበሰበ የቅድመ ምርጫ ውጤት ዶናልድ ትራምፕን እየመሩ ይገኛሉ።
ሆኖም ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ በቀጣዮቹ 75 ቀናት ልዩነቱን የማጥበብ እድል እንዳላቸው ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.