Fana: At a Speed of Life!

በተፋሰሱ ሀገራት ከሚገኙ የዳያስፖራ አባላት ማህበረሰብ ጋር በግድቡ ድጋፍ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በተፋሰሱ ሀገራት ከሚገኙ የዳያስፖራ አባላት ማህበረሰብ ጋር በታላቁ ህዳሴ ግድቡ ድጋፍ ዙሪያ ውይይት መካሄዱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባዩ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው በሀገራቱ ካሉ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በግድቡ ድጋፍ ዙሪያ ውይይት ማካሄዳቸውን ገልጸዋል።

የዳያስፓራ አባላቱም ድጋፉቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መግለጻቸውን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

በተጨማሪም የዳያስፓራ ሚኒስትር ዲኤታ በጅቡቲ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ከሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ውይይት አድርገዋል ብለዋል።

በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ የኢትዮጵያውኑን መብት ለማስጠበቅ እየተሰራ ነው ያሉት አምባሳደር ዲና ከቤሩት ቆንስላ ጋር በመተባበር 80 ለሚሆኑ ዜጎች ሰነድ ተዘገጅቶላቸዋል ብለዋል።

ከሳዑዲ መንግስት ጋር የተሻለ መቀራረብ አለ ያሉት አምባሳደር ዲና የዜጎቹን መብት ለማስጠበቅ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ ተደርሷልም ነው ያሉት ፡፡

በተጨማሪም በኮቪድ19 የተጎዳው የቱሪዝም ዘርፍ በሚሻሻልበት ሁኔታ ላይ ከዘርፉ አካላት ጋር ውይይት መደረጉን ጠቅሰዋል።

በሀብታሙ ተክለስላሴ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.