Fana: At a Speed of Life!

በህንድ በአንድ ቀን ብቻ ከ69 ሺህ በላይ ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በህንድ በአንድ ቀን ብቻ ከ69 ሺህ በላይ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተነገረ፡፡

ይህንንም ተከትሎ በሃገሪቱ በአጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 3 ሚሊየን ተጠግቷል ነው የተባለው፡፡

በህንድ እስካሁን 55 ሺህ 950 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ሲዳረጉ 2 ሚሊየን 223 ሺህ 202 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገም ችለዋል ነው የተባለው፡፡

ሃገሪቱ አሁን ከአሜሪካ እና ብራዚል በመቀጠል ቫይረሱ በብዛት የተገኘባት ሃገር ሆናለች፡፡

እንዲሁም ከአለም በቫይረሱ ሳቢያ በብዛት ሞት የተመዘገበባት አራተኛ ሃገር መሆኗም ታውቋል፡፡

ሆኖም የሕንድ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሃገሪቱ በየቀኑ 1 ሚሊዮን ለሚሆኑ ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ እያደረገች መሆኑን ገልፀው ከቫይረሱ የሚያገግሙ ሰዎች ቁጥርም በፍጥነት መጨመሩን ተናግረዋል፡፡

አሁን በዓለም 23 ሚሊየን 148 ሺህ ሰዎች ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሲሆን፥ 15 ሚሊየን 148 ሺህ 526 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡

803 ሺህ 784 ሰዎች ደግሞ በቫረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.