Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና የሳዑዲ አረቢያ የልማት ፈንድ የ140 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ እና የሳዑዲ አረቢያ የልማት ፈንድ የ140 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የብድር ስምምነት በዛሬው እለት ተፈራርመዋል።

የብድር ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ እና የሳዑዲ አረቢያ የልማት ፈንድ ምክትል ሊቀ መንበር ካሊድ አልክሁድራ ናቸው የተፈራረሙት።

ብድሩም በአነስተኛ ወለድ በረጅም ጊዜ የሚከፈል መሆኑም ተገልጿል።

ከብድር ስምምነቱ 75 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላሩ ከደብረ ማርቆስ- ሞጣ ለሚገነባው የመንገድ ፕሮጀክት የሚውል ሲሆን፥ የመንገድ ፕሮጀክቱም 118 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ነው።

የስምምነቱ ሁለተኛ አካል የሆነው 65 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ደግሞ ለዋን ዋሽ ብሄራዊ ፕሮግራም የሚውል መሆኑም ነው የተገለፀው።

በአላዛር ታደለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.