Fana: At a Speed of Life!

በጤናው ዘርፍ ላይ ያተኮረ የስርዓተ ጾታ ፎረም ተቋቋመ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጤና ሚኒስቴር በጤናው ዘርፍ ላይ ያተኮረ የስርዓተ ጾታ ፎረም መቋቋሙን አስታወቀ።

የጤና ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት፣ አጋር ድርጅቶች፣ ባለድርሻ አካላት፣ ኤጀንሲዎችና ሆስፒታሎች የፎረሙ አባላቶች ናቸው ተብሏል።

የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ሰሀረላ አብዱላሂ የፎረሙ መመስረት የእናቶችና ህጻናትን ሞት ለመቀነስ፣ የሴቶችን እኩልነት ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጾታዊ ጥቃቶችን ከመከላከል እና መረጃን መሰረት ያደረጉ ጥናቶችን ከማድረግ አኳያ ባለፉት ጊዜያት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውንም ገልጸዋል።

ሚኒስትሯ አያይዘውም እነዚህን ስራዎች በጋራ በመስራት ያለውን በጀትም ሆነ አቅም አሟጦ በመጠቀም በጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በፎረም መደራጀት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

ፎረሙ መመስረቱ በርካታ ጠቀሜታዎች ያሉት ቢሆንም በተለይም በሚደረጉ የእርስ በርስ ውይይቶች የአቅም ክፍተቶችን ለመሙላት ትልቅ ሚና እንዳለው መገለጹን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.