Fana: At a Speed of Life!

የኢንዱስትሪ ፓርኮች በቴክኖሎጂ ሽግግር በሚፈለገው ደረጃ እየሄዱ አለመሆናቸው ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች በወጪ ንግድና ስራ እድል ፈጠራ እየተሻሻሉ ቢሆኑም በቴክኖሎጂ ሽግግር በሚፈለገው ደረጃ እየሄዱ አለመሆናቸውን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገለጸ።

የአምስት ዓመታትን እድሜ የያዘው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት፥ ዛሬ ላይ በሀገሪቱ የተለያዩ ከተሞች የተገነቡትን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ብዛት 12 አድርሷል።

ከእነዚህ ውስጥ ሰባት የኢንዱስትሪ ፓርኮች በስራ ላይ ሲሆኑ፥ ቀሪዎቹ ደግሞ በተለያየ የግንበታ ሂደት ላይ ይገኛሉ።

በቅርቡ የተመረቁት እንደ ጅማ እና ደብረ ብርሃንን የመሳሰሉ የኢንዱሰትሪ ፓርኮች ደግሞ በማሽን ተከላና ሰራተኞችን በማሰልጠን ሂደት ላይ መሆናቸው ታውቋል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ሌሊሴ ነሜ ከፋና ብሮድካስቲንግ ጋር ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ የኢንዱሰትሪ ፓርኮች ከተቋቋሙባቸው በት ዋነኛ አላማ ዎች ውስጥ አንዱ ከሆነው የወጪ ንግድ አፈጻጸም ጋር በተያያዘ ባለፉት 5 ወራት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች በተላኩ ምርቶች ከ65 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል።

ገቢው ከዓመት ዓመት መሻሻሎችን እያሳየ መምጣቱን የሚገልጹትወይዘሪት ሌሊሴ ፥ለውጤቱ ከሎጂስቲክስ ጋር የተያያዙ ነገሮች ላይ መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

ፓርኮቹ እየፈጠሩ ያሉት አዳዲስ የስራ እድልም በየጊዜው እያደገ ነው ያሉት ስራ አስፈጻሚዋ፥ አሁን ላይ ፓርኮቹ ከ65 ሺህ በላይ የስራ እድል ፈጥረዋል ነው ያሉት ።

ከነዚህም ሀዋሳ ኢንዱሰትሪ ፓርክ ብቻውን 33 ሺህ ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩን ነው የገለፁት።

ሌላው ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት የሚጠበቀው የማምረቻ ዘርፉን ቀጠይነት ለማረጋገጥ የሚያግዘው የቴክኖሎጂ ሸግግር ሲሆን፥ ይህ ግን አሁንም አንቅፋቶች እየጋጠሙት መሆኑን ነው ዋና ስራ አስፈጻሚዋ የሚናገሩት።

ሽግግሩ ምንም እንኳን በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ጥሩ በሚባል ደረጃ እየተከናወነ ቢሆንም፤ የእውቀት ሽግግሩን ለማስፋት በሚል ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር እንዲተሳሰር የተያዘው አቅጣጫ ውጤታማ እየሆነ አደለም ይላሉ።

ችግሩን አስካሁን በተመጣበት መንገድ ለመፍታታት አለመቻሉን ያነሱት ወይዘሪት ልሊሴ፥ አሰራሩን በህግ የታሰረ ለማድረግ በአሁኑ ወቅት ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር የመግባቢያ ስምምነት ፊርማዎች እየተፈረሙ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በትዕግስት አብርሃም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.