Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቅ ሀገሪቱ ያላትን ተስፋ ያመላክታል – የአዲስ አበባ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቅ ሀገሪቱ ያላትን ተስፋ እንደሚያመላክት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለፁ።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት ነዋሪዎቹ በሳተላይቷ መምጠቅ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

አስተያየት ሰጭዎቹ ሳተላይቷ ከግብርና ጋር የተያያዙ ጥናትና ምርምሮችን ጨምሮ ሌሎች ስራዎች ለመስራት የሚያግዙ መረጃዎችን መስጠቷ መጭውን ጊዜ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ወደ ብልጽግና የሚደረገውን ጉዞ ያሳካል ብለዋል።

ዶክተር እሌኒ ገብረመድህን የሳታላይት ምጥቀቱ ለሀገር ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን በመግለፅ፥ ዓለም ከምድራዊው ሩጫው በላይ በህዋ ውድድር የሚገኝ በመሆኑ ይህ ጅምር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ነው ያሉት።

ለነገው የተሻለ ስራም የዛሬው ጅምር መቀጠል እንደሚኖርበትም አንስተዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር አህመድ መሀመድ በበኩላቸው፥ በዛሬው ስኬት መላው ኢትዮጵያውያን ሊደሰቱ እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

ዛሬ ማለዳ ላይ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የሳተላይቷን ወደ ህዋ መምጠቅ አስመልክቶ የፎቶና የስዕል አውደ ርዕይ ተካሂዷል።

በሀይለየሱስ መኮንን እና ዘቢብ ተክላይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.