Fana: At a Speed of Life!

በዚህ ዓመት በሊቢያ ቢያንስ 284 ዜጎች ሞተዋል-ተመድ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2012(ኤፍቢሲ) በሊቢያ በዚህ አመት ቢያንስ 284 ሰዎች መሞታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡

የተባበሩት መንግስታት  ድርጅት ይፋ ባደረገው ሪፓርት በሊቢያ  የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተባባሰ መሆኑን ነው ያስታወቀው፡፡

በተመድ  የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽን ቃል አቀባይ  ሩፔርት ኮልቪል “ በዚህ ዓመት የተመዘገበው ሞት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር  ከአንድ አራተኛ በላይ ብልጫ አሳይቷል” ብለዋል ፡፡

በሰላማዊ ሰዎች ፣ በሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና ጋዜጠኞች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ፣ የስደተኞች አያያዝ እንዲሁም እስራት አሳሳቢ እንደሆኑ ጠቅሰዋል ፡፡

ለበርካታ ሰዎች ህይወት ህልፈት በመሆነው የአየር ጥቃት 182 ሰዎች ሲሞቱ 212 ሰዎች ጉዳት እንዳጋጠማቸው ነው የተነገረው፡፡

ቃል አቀባዩ እንዳሉት በግጭቱ ምክንያት 343 ሺህ ዜጎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውና 100 ሺህ ዜጎች የመፈናቀል ስጋት እንዳለባቸው አንስተዋል፡፡

ምንጭ፣ www.middleeastmonitor.com

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.