Fana: At a Speed of Life!

የፈረንሳይ ወታደሮች በማሊ ባካሄዱት የጸረ ሽብር ዘመቻ 33 ታጣቂዎች ተገደሉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ ሲ) የፈረንሳይ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች በማሊ ባካሄዱት የጸረ ሽብር ዘመቻ 33 ታጣቂዎች መገደላቸው ተገልጿል።

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት በትናንትናው ዕለት ኮቲዲቯር ገብተዋል።

በጉብኝታቸው ወቅትም የሀገራቸው ወታደሮች በትናንትናው ዕለት በማሊ ሞፕቲ ግዛት ባከሄዱት የጸረ ሽብር ዘመቻ 33 ጂሃዲስት ታጣቂዎች መገደላቸውን አስታውቀዋል።

በተጨማሪም በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር የነበሩ ሁለት የማሊ ፖሊስ ኦፊሰሮችን ማስለቀቅ መቻሉን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፥ለስኬታማ የጸረ ሽብር ዘመቻው ወታደሮችን አመስግነዋል።

በሳህል ቀጠና የሚንቀሳቀሱ የሽብር ቡድኖችን በዘላቂነት ለማስወገድም ከአካባቢው ሀገራት ጋር በቅንጅት የሚሰራ መሆኑን አንስተዋል።

ለዚህም ባሳለፍነው ዓርብ ዕለት በቀጠናው ሽብርተኝነትን መከላከል የሚያስችል አዲስ የጦር ሃይል ለማቋቋም እንደሚሰራ መናገራቸው ይታወሳል።

ፈረንሳይ በምዕራብ አፍሪካ የሚስተዋለውን የሽብር እንቅስቀሴ ለመቆጣጠር በፈረንጆቹ 2013 ጀምሮ 4 ሺህ 500 ባላይ ወታደሮቿን በስፍራው አሰማርታለች።

ምንጭ፦ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.