Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ከሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሌተናል ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ የተካሄደውም የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ የውሃ ጉዳይ የሚኒስትሮች በሱዳን ካርቱም እያኬዱት ባለው የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ውይይት ጎን ለጎን ነው።

በውይይታቸውም የሀገራቱን ግንኙነት የጋራ ተጠቃሚነትን ባስከበረ መልኩ ይብልጥ ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.