Fana: At a Speed of Life!

የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የኦሮሚያ ክልል ገለፀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢሬቻ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን የኦሮሚያ ክልል አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ፡፡
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል የተለየ ገጽታ እንደሚኖረው ያስታወቀው ቢሮው÷ በበዓሉ ላይ በክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እንዲሁም በአባገዳዎች ተመልምለው ጥሪ የሚደረግላቸው አካላት ብቻ እንደሚገኙ የክልሉ የአስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጅብሪል መሐመድ ገልፀዋል፡፡
በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ዜጎችም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር የሚያስቡ አካላት ካሉም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አቶ ጅብሪል አሳስበዋል፡፡
ይህን ማሳሰቢያ ችላ ብለው ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት በሚሞክሩ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የቢሮ ኃላፊው ማስጠንቀቃቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.