Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ሰመራ ዩኒቨርሲቲና እና ዱብቲ ሆስፒታልን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ እና በዱብቲ ሆስፒታል ጉብኝት አድርገዋል።

ፕሬዚዳንቷ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ባደረጉት ጉብኝት ከዩኒቨርሲቲው ከተውጣጡ ሴት ተማሪወች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

በተጨማሪም በሰመራ ከተማ የሚገኘውን የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት በመጎብኘት የማስፋፊያ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

በተመሳሳይ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በዱብቲ ወረዳ የሚገኘውን የዱብቲ ሆስፒታል መጎብኘታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል

በዚህም በከተማዋ የሚገኙ ከኤች አይ ቪ/ኤድስ ጋር የሚኖሩ ዜጎች ማህበራትን እንቅስቃሴ ተመልክተዋል።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሰመራ በሚከበረው የኤች አይ ቪ/ኤድስ ቀን ላይ ለመሳተፍ በትናንትናው ዕለት አፋር ክልል ሰመራ ከተማ መግባታቸው ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.