Fana: At a Speed of Life!

ደቡብ አፍሪካ ድንበሮቿን ለአፍሪካ ሀገራት ክፍት አደረገች

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 21 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ደቡብ አፍሪካ ከኮኖና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ባለፈው መጋቢት ወር የዘጋችውን ድንበር ለአፍሪካ ሀገራት ክፍት አድርጋለች።
ከመላው አፍሪካ ለሚመጡ መንገደኞች ድንበሯን ክፍት ያደረገች ሲሆን÷ ነገር ግን ብሪታንያ፣ አሜሪካና ሩሲያን ጨምሮ በከፍተኛ ደረጃ ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ ከሆኑ ሃገራት የሚመጡ መንገደኞች ላይ እገዳው አለመነሳቱም ተገልጿል።
በዚህም በዛሬው እለት የተወሰኑ የየብስ ድንበሮቿንና ኬፕታውን፣ደርባን እና ጆሀንስበርግ ያሉትን አውሮፕላን ማረፊያዎቿን ክፍት አድርጋለች።
የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶር÷ ወደ ሀገሪቱ የሚመጡ ሁሉም መንገደኞች ከመጡበት ሃገር ከኮኖና ቫይረስ ነጻ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የህክምና ሰርተፊኬት ያስፈልጋቸዋል ብለዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ደቡብ አፍሪካ ሲደርሱ ምርመራ ይደረግላቸዋልም ነው ያሉት።
የኮሮና ቫይረስ ምልክት የሚያሳዩ ወይም በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ለህክምና የሚያስፈልገውን ወጪ እንደሚሸፍኑም ጠቅሰዋል ።
አያይዘውም የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ ከሆነባቸው ሀገራት ዲፕሎማቶች፣ ባለሃብቶች እና ነጋዴዎች ብቻ አስፈላጊው ምርመራ ተደርጎላቸው እንደሚገቡም ገልጸዋል፡፡
ደቡብ አፍሪካ 674 ሺህ የሚሆኑ ዜጎቿ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን ይህም ከአፍሪካ ቀዳሚውና የአህጉሪቱን ግማሽ ይሸፍናል።
ምንጭ፥ ቢቢሲ
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.