Fana: At a Speed of Life!

የኢሬቻ በዓል በሆራ ፊንፊኔ ተከበረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኦሮሞ ገዳ ሥርዓት አካል የሆነው የኢሬቻ በዓል በሆራ ፊንፊኔ ተከበረ።
የበዓሉ ስነ ስርዓት የተጀመረው በገዳ ሥርዓት መሰረት በአባገዳዎች ምርቃት ነው፡፡
በበዓሉ ላይ ለመታደም ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ሆራ ፊንፊኔ በማቅናት በባህሉ መሰረት ለፈጣሪያቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ከአዲስ አበባ እና ከዙሪያዋ እንዲሁም ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች ለበዓሉ በባህል አልባሳት ደምቀው በሆራ ፊንፊኔ በመገኘት ኢሬቻውን በአንድነት መንፈስ በጋራ አክብረውታል፡፡
የኢሬቻ በዓል የምስጋና፣ የፍቅር፣ የሰላም፣ የእርቅና የይቅርታ በዓል ነው።
ኢሬቻ የምስጋናና የምልጃ በዓል ሲሆን በዚህ በዓል የኦሮሞ ሕዝብ ሁሉን ነገር ለፈጠረው ምድርንና ሰማይን፣ ወንዝንና ባህርን፣ ቀንንና ሌሊትን፣ ብርሀንና ጨለማን፣ ሕይወትና ሞትን፣ ክረምትንና በጋን፣ ዝናብንና ሐሩርን፣ ዕጽዋትን፣ እንስሳትንና ሰውን ለፈጠረ፤ ሁሉን ነገር ማድረግ ለሚችል ዋቃ (አምላክ) ምስጋናና ክብር የሚያቀርብበት በዓል ነው።
 
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.