Fana: At a Speed of Life!

የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የመክፈቻ ሥነ-ስርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣መስከረም 25 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 5ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ስርዓት ጉባኤ ተካሄደ።
ጉባኤው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በሚገኘው የስብስባ አዳራሽ ነው የተካሄደው።
የሁለቱ ምክር ቤቶችን የጋራ ስብሰባም የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ያስጀመሩት ሲሆን የ2013 የፌደራል መንግስቱ ልዩ ትኩረቶችን የሚዳስሰው የመክፈቻ ንግግራቸውን አቅርበዋል፡፡
በመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የሀይማኖት አባቶች፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ታዋቂ ሰዎች እና አምባሳደሮች እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚገኙ ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቷ በመክፈቻ ንግግራቸው፦

  • ያለፈው አመት ስኬታማ እንደነበር አንስተዋል፣
  • ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኢትዮ ኤርትራን ግንኙነት ዳግም በማደስ የኖቤል የሰላም ሽልማት ማሸነፋቸው፣
  • በህዳሴ ግድብ ዙሪያ በተሰሩ ስራዎችና የህዳሴው ግድብ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት፣
  • ሲንከባለሉ የቆዩ ፕሮጄክቶችን በስኬት ማጠናቀቅ የተቻለበትና ትልቅ ተሞክሮ እንደተገኘበት ጠቅሰዋል
  • በተጨማሪም ካለፉት አመታት በተሻለ የወጪ ንግድ ገቢ የተገኘበት መሆኑ፣
  • 5 ቢሊየን ችግኝ በመትከል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ማሳካት የተቻለበት፣
  • ለሶስት ሚሊየን ወጣቶች የስራ እድል መፈጠሩ፣
  • የሃገሪቱ የ10 አመት የሃገሪቱ ፍኖተ ብልፅግና የተዘጋጀበት፣
  • በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር መድረክ በመፍጠር ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራ መሰራቱ ፣
  • ኮሮናን በመከላከል ረገድ አፋጣኝ የመከላከል አቅም የተገነባበት መሆኑ፣
  • በኮሮና ምክንያት የሚፈጠረውን የምግብ እጥረት ለመቋቋም ምንም መሬት ጦሙን እንዳያድር ማድረግ የተቻለበት፣
  • አመቱ በጥቅሉ በርካታ ታሪካዊ ስኬቶችን የተስተናገደበት ነበር፣
  • ከስኬቶቹ ባሻገር በርካታ ተግዳሮቶች የታዩበት ነበር፣
  • ከዚህ ውስጥ በኮቪድ19 ምክንያት ሃገራዊ ምርጫ መራዘም፣
  • በተፈጠሩ ግጭቶች የዜጎች ህይዎት የጠፋበትና ብሎም የተፈናቀሉበት፣
  • ያልተገቡ የህግ ጥሰቶች የተፈጸሙበት፣
  • የበረሃ አንበጣ በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች ጉዳት ያደረሰበትና በርካታ አጋጣሚዎች የተከሰተበት እንደነበር ጠቅሰዋል።

 

 

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.