Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አምስት ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ ክልል ለመመስረት ያቀረቡት ጥያቄ በሙሉ ድምጽ ጸደቀ

አዲስ አበባ፣መስከረም 26፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አምስት ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ በጋራ አንድ ክልል ለመመስረት ያቀረቡት ጥያቄ በሙሉ ድምፅ መጽደቁ ተገለጸ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኙ አምስት ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ በጋራ አንድ ክልል ለመመስረት ቀደም ሲል ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥያቄ አቅርበው እንደነበር ተገልጿል።

በዚህም መሰረት ምክር ቤቱ ሰፋ ያለ ውይይት ካደረገ በኋላ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስፈጻሚነት ሕዝበ ውሳኔ እንዲደራጅ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

ጥያቄውን ያቀረቡት የከፋ፣ ቤንች፣ ሸኮ ፣ምዕራብ ኦሞ፣ ዳውሮ፣ ሸካ ዞኖችና የኮንታ ልዩ ወረዳ ናቸው ተብሏል።

ዞኖቹ ተቀራራቢ ቋንቋ፣ ባሕል፣ ታሪክና መልካምድራዊ አቀማመጥ ስላለን አንድ ላይ ብንሆን የተሻለ ነው በማለት ጥያቄ አቅርበው እንደነበር ኢዜአ ዘግቧል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.