Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች አልጋወራሽ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 14፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች አልጋወራሽ ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ነኸያን ጋር ተወያይተዋል።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በትናንትናው ዕለት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች አቡ ዳቢ ገብተዋል።

በቆይታቸውም ከሀገሪቱ አልጋወራሽ ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ነኸያን፣ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ፕሬዚዳንታዊ ጉዳዮች ተጠሪ ሼክ መንሱር ቢን ዛይ እና ከጦር ሃይሎች ምክትል አዛዥ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም የሀገራቱን የሁለትሽ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል ገልጸዋል።

ከዚህ ባለፈም በተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች በተለይም  በግብርና እና ኢነርጂ ዘርፎች ላይ በትብብር እና በቅንጅት መስራት በሚችሉባቸው መንገዶች ላይ በትኩረት መክረዋል።

በዚህም የሀገራቱን ታዳሽ ሃይል እና የግብርና ዘርፍ ማሳደግ እና ማዘመን የሚያስችሉ ስምምነቶች መፈራረማቸው ተመላክቷል።

በተጨማሪም በቅርቡ የተስተዋሉ ቀጠናዊ እና ዓለማቀፋዊ ለውጦች የጋራ ተጠቃሚነትን ባስከበረ መልኩ በዘላቂነት ማስቀጠል በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸው ነው የተገለጸው።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.