Fana: At a Speed of Life!

የብራዚሉ ፕሬዚዳንት ጃዬር ቦልሶናሮ ሆስፒታል ገቡ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 14፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የብራዚሉ ፕሬዚዳንት ቦልሶናሮ በፕሬዚዳንታዊ ቤተ መንግስት ውስጥ መውደቃቸውን ተከትሎ ሆስፒታል መግባታቸው ተሰምቷል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ብራዚሊያ በሚገኘው  መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ድንገት መውደቃቸውን ተከትሎ  ሆስፒታል መግባታቸው ተነግሯል፡፡

በአልቮራዳ ቤተ መንግስት የወደቁት ጃዬር ቦልሶናሮ  በፕሬዚዳንቱ የህክምና ቡድና  ህክምና ከተሰጣቸው በኋላ ወደ ሀገሪቱ ጦር  ሆስፒታል ተወስደው ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝም የፕሬዝዳንቱ ቃል አቀባይ ፅህፌት ቤት አስታውቋል፡፡

ምንም አይነት ለውጥ  አልታየባቸውም የተባለው ፕሬዚዳንቱ  የጭንቅላት ምርምራ እንደተረገላቸው  መግለጫው አመልክቷል፡፡

ፕሬዚዳንቱ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው በሚገኘው ሆስፒታል የተገኙት የደህንነት ተቋም ሚኒስትር አጉስቶ ሄሌኖ ፕሬዚዳንቱ ደህና ናቸው ሆኖም የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይቆያሉ ብለዋል፡፡

ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤቱ ያወጣው መግለጫ እንደሚያመለክተው ቀኝ ዘመሙ  የብራዚል ፕሬዚዳንት  ጃዬር ቦልሶናሮ ከ6 እስከ 12 ሰዓታት የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይቆያሉ ብሏል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ባለፈው ዓመት በምርጫ  ዘመቻ ላይ በነበሩበት ወቅት  በስለት ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው እንደነበር ይታወሳል ፡፡

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ጤንነታቸው አሳሳቢ  የሆነው ፕሬዚዳንቱ በተደጋጋሚ ቀዶ ህክምና ሲያደርጉ ቆይተዋል ተብሏል፡፡

 

ምንጭ፡-አልጀዚራ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.