Fana: At a Speed of Life!

በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የተገነባው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 28 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) በደቡብ ወሎ ዞን አልቡኮ ወረዳ በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በ21 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ ተመረቀ።

በዞኑ አልቡኮ ወረዳ ጦሳ ፊላና ቀበሌ የተገነባው አጠቃላይ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታው የተጀመረው በ2011 ዓ.ም እንደሆነም ታውቋል።

ትምህርት ቤቱ 18 የመማሪያ ክፍሎች፣ ሁለት ቤተ ሙከራዎችና ቤተ መጻሕፍት አለው ተብሏል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ይልቃል ከፋለ እና ሌሎች የክልሉና የዞኑ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት ከዚህ ቀደም በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ትምህርት ቤቶችን አስገንብቶ ማስመረቁ ይታወሳል፡፡

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.