Fana: At a Speed of Life!

ጎጉል እና አፕል ለስለላ ጥቅም ላይ ይውላል ያሉትን የቶቶክ መተግበሪያ አስወገዱ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጎጉል እና አፕል ለስለላ ጥቅም ላይ ይውላል በማለት የጠረጠሩትን የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን መተግበሪያ ቶቶክን ማስወገዳቸው ተገለፀ፡፡

ቶቶክ የተሰኘው ይህ መተግበሪያ ሰዎች በቀላሉ በተንቀሳቃሽ ምስል እና በፅሁፍ  እንዲያወሩ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

ኔውዮር ታይምስ አንደዘገበው ከዋትስ አፕ ጋር ተመሳሳይ አገልግሎት የሚሰጠው ቶቶክ  በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት ለስለላ መሳሪያት ጥቅም ላይ ይውላል ተብሏል፡፡

ኔውዮርክ ታይምስ የአሜሪካ ባለስልጣናትን ጠቅሶ በዘገባው እንዳሰፈረው ቶቶክ የተሰኘው መተግበሪያ ለተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሰላዮች የተጠቃሚዎችን ውይይት ፣ እንቅስቃሴ  እና ፎቶ መሰል የግል መረጃዎች  አሳልፎ ይሰጣል፡፡

ጎግል ይህን መተግበሪያ ባለፈው ሀሙስ ማጥፋቱ የተገለፀ ሲሆን አፕልም  ጎግልን በመከተል በቀጣዩ ቀን ከመተግበሪያ ዝርዝሮቹ ውስጥ ማጥፋቱ ተጠቁሟል፡፡

ቶቶክ መተግበሪያ ለተጠቃሚዎቹ በቅርቡ በአፕ ስቶር እንደሚመለስ  አስታውቋል፡፡

ኩባንያው ባስተላለፈው መልዕክት በጎግል ስቶር እና በአፕል ስቶር በጊዜያዊነት እንደማይገኝ የገለፀ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ የቴክኒክ ጉዳይ መሆኑን ገልጿል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

በፌቨን ቢሻው

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.