Fana: At a Speed of Life!

የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ከኳታር የትራንስፖርት እና ኮሙዩኒኬሽን ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ከኳታር የትራንስፖርት እና ኮሙዩኒኬሽን ሚኒስትር ጃሲም ሲይፍ አህመድ አል ሱላይቲ ጋር ተወያዩ።
በቪዲዮ ኮንፈረንስ በተካሄደው በዚህ ውይይት ሁለቱ ሀገራት በዘርፉ ያላቸውን ትብብር በተመለከተ ግምገማ አድርገዋል።
በዚህም ሚኒስትሮቹ በኮሙዩኒኬሽን፣ ትራንስፖርት እና በሲቪል አቪየሽን ዘርፎች ሀገራቱ ባላቸው ትብብር ዙሪያ ምክክር አድርገዋል።
እንዲሁም በእነዚህ ዘርፎች ሀገራቱ ትብብራቸውን የበለጠ ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸው ገልፍ ታይምስ ዘግቧል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.