Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ አርመንያንና አዘርባጃንን ልታሸማግል ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሩሲያ በናጎርኖ ካራባህ ክልል ወደ ጦርነት የገቡትን አርመንያንና አዘርባጃንን ልታሸማግል መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ሁለቱ ሃገራት ከሳምንት በፊት ወደ ጦርነት መግባታቸው ይታወሳል፡፡

አሁን በሞስኮ ሊደረግ የታሰበው የሃገራቱ ውይይት ወደ ጦርነት ከገቡ በኃላ የመጀመሪው ነው ተብሏል፡፡

በዚህ ውይይት አማካኝነት ሃገራቱ ወደ ተኩስ አቁም ስምምነት ይገባሉ የሚል ተስፋን አጭሯል፡፡

ከሩሲያ በተጨማሪ ፈረንሳይና አሜሪካም የማሸማገል ጥረቱ ላይ እንደሚሳተፉም ነው የተገለጸው፡፡

በሁለቱ ሃገራት መካከል የተነሳው ጦርነት አሁንም መቀጠሉን ሞስኮ ታይምስ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.