Fana: At a Speed of Life!

በመስከረም ወር ብቻ ከ10 ሺህ በላይ ህግ እና ደንብ የተላለፉ አሽከርካሪዎች ተቀጥተዋል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባሳለፍነው መስከረም ወር ብቻ ከ10 ሺህ በላይ የትራፊክ ህግ እና ደንብ የተላለፉ አሽከርካሪዎች መቅጣቱን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡
ኤጀንሲው በመስከረም ወር ብቻ የትራፊክ ህግ እና ደንብን ለማስከበር ባደረገው የቁጥጥር ስራ 10 ሺህ 711 የትራፊክ ደንብ የተላላፉ አሽከርካሪዎች መቅጣቱ ታውቋል፡፡
በተደረገው የቁጥጥር ስራም ፍፁም መቆም የሚከለክሉ ቦታዎች ላይ መቆም፣ የትራፊክ መብራት መጣስ፣ ባልተፈቀደ ተቃራኒ አቅጣጫ ማሽከርከር፣ የባስ ፌርማታዎች ላይ መቆም፣ የዩተርን ክልከላን አለማክበር፣ አደባባዮች እና የትራፊክ መብራት ላይ ግብይት መፈፀም፣ ዜብራ እና መጋጠሚያ መንገዶች ላይ መቆምና የደንብ መተላለፎች መሆናቸውም ታውቋል፡፡
እንዲሁም የተሽከርካሪን ፍሰት በሚያውክ መልኩ በሰያፍ መቆም፣ ለጊዜያዊ ማቆሚያነት የተፈቀዱ መንገዶች ላይ ደርቦ ማቆም እና የመሳሰሉት የደንብ መተላለፎች እንደሚገኙበትም ኤጀንሲው ገልጿል፡፡
ኤጀንሲው በከተማዋ የሚስተዋለውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ፣ ፍሰቱ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ዘመናዊ የትራንስፖርት ስርዓት ለመገንባት ከማሻሻያ ስራዎች በተጨማሪ የትራፊክ ህግ እና ደንብ እንዲከበር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ላይ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.