Fana: At a Speed of Life!

የደህንነት ፍተሻ መስፈርት አሟልቶ እንዳይገባ የተከለከለ ሰው አልባ በራሪ ቁስ የለም

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 3 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሚጠበቅበትን የደህንነት ፍተሻ መስፈርት አሟልቶ እንዳይገባ የተከለከለ ሰው አልባ በራሪ ቁስ (ድሮን) አለመኖሩን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛዉ ገለጹ፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ ይህን የተናገሩት ዛሬ በኤጀንሲው ለጋዜጠኞች ስለ በተቋማዊ ሪፎርም እና ቀጣይ የአምስት ዓመት የትኩረት አቅጣጫ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡
ድሮን ወደ ሃገር ወስጥ ሲገባ የራሱ የሆነ የአሰራር ስርዓት ውያነሱት ዋና ዳይሬክተሩ በሀገሪቱ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የትግራይ ክልልን ጨምሮ የተለያዩ ክልሎች ድሮኖችን ለማስገባት ጥያቄ አቅርበው በመመሪያው መሰረት እየተስተናገዱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ወደ ትግራይ ክልል ድሮን እንዳይገባ ተደርጓል የተባለው ጉዳይም በመጀመሪያ ደረጃ ድሮኑ ጥናት እና ሪቨርስ ኢንጂነሪነግ ዓላማ በሚል የመጣ መሆኑን ጠቅሰው በመቀጠልም ድሮኑ ለጸረ-ዓረም ኬሚካል መርጫ ዓላማ እንደሚውል የተገለፀ ሲሆን ከሰሞኑ ደግሞ ለአንበጣ መንጋ መከላከል
ማ በሚል መጠየቁን አንስተዋል፡፡
ኤጀንሲው በድሮኑ ላይ የደህንነት ፍተሻ ባደረገበት ወቅት ድሮኑ የአጠቃቀም እና ተጓዳኝ ጉዳዮች መግለጫ የሌለው ከመሆኑ ባሻገር ከእስራኤል እንደተላከ ቢገለጽም ምርቱ ግን ከቻይና እንደሆነ በዚሁ ወቅት መታወቁን መግለጻቸውን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ሆኖም የድሮኑ ትክክለኛ ዓላማ እና የሚሰጠውን አገልግሎት የደህንነት ተጋላጭነትን የሌለው መሆኑን ማጣራት የኤጀንሲው ሃላፊነት መሆኑን ያወሱት ዋና ዳይሬክተሩ ለአንበጣ መከላከል ተብሎ የተጠየቀው ድሮን የደህንነት ፍተሻ አሟልቶ ባለመገኘቱ ፍቃድ ያልተሰጠው መሆኑን አስረድተዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.