Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎች የታዳሽ ሀይልን ለማቅረብ የሚያስችል የ1 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሮኪ ማውንቴን ኢንስቲቲዩት በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎች የታዳሽ ሀይል ለማቅረብ 1 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ማግነቱን አስታወቀ።
ኢንስቲቲዩቱ እንዳስታወቀው ከኔዘርላንድሱ አይ ኬ ኢ ኤ ፋውንዴሽን የተገኘው ድጋፍ የታዳሽ ሀይልን በገጠራማው ኢትዮጵያ ክፍል ከማቅረብ ባሻገር
የአሌክትሪክ ሀይል በአግባቡ በመጠቀም ተጨማሪ ገቢ ማስገኘትን አላማ ያደረገ ነው።
ድጋፉ በማህበረሰቡ ውስጥ የኢኮኖሚ ልማትን በማሳደግ በገጠራማው የሀገሪቱ ክፍል የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ውጤታማ እንደሚያደርግ ነው የሮኪ ማውንቴን ኢንስቲቲዩት ያስታወቀው።
የታዳሽ ሀይል አቅርቦትን ከዘላቂ የኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦት ጋር በማጣመር ውጤታማ የማድረግ ፍላጎት እንዳለው ድጋፉን ያደረገው አይ ኬ ኢ ኤ ፋውንዴሽን ገልጿል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.