Fana: At a Speed of Life!

አቶ ልደቱ አያሌው በተከሰሱበት ህገወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ወንጀል ሶስት የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ተሰሙ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ ልደቱ አያሌው በተከሰሱበት ህገወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ወንጀል ሶስት የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ተሰሙ።

ዛሬ ረፋድ ላይ በአዳማ ምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው ሶስት የዐቃቤ ህግ ምስክሮች የምስክር ቃላቸው የተሰማው።

ፍርድ ቤቱም የሰማውን ምስክርነት መርምሮ ብይን ለመስጠት ለጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠ ሲሆን፥ ተከሳሹ የተፈቀደላቸው የ100 ሺህ ብር ዋስትናን ተከትሎ ለምን እንዳልተፈቱ የጠየቀ ሲሆን የቢሾፍቱ ፖሊስ ሃላፊ ቀርቦ እንዲያብራራ የታዘዘውን ትዕዛዝም ተመልክቷል።

በትዕዛዙም የቢሾፍቱ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ተቀይሯል መባሉን ተከትሎ ተወካይ ወይም የክፍል ሃላፊ ለምን እንዳልቀረቡ በቀጣይ ቀጠሮ ቀርበው እንዲያብራሩም ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽንም ግለሰቡ በህገወጥ ጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ክስ በተፈቀደላቸው የ100 ሺህ ብር ዋስትና መሰረት ከእስር እንዲፈታቸውም ፍርድ ቤቱ አዟል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አቶ ልደቱ አያሌው ህገመንግስቱን ለመናድ በማሰብ የተለያዩ ህገ መንግስቱን የሚቃረኑ የሽግግር ሰነዶችን በማዘጋጀት ወንጀል የቀረበባቸውን ክስ በችሎት ለማንበብ ለነገ አርብ ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱ ይታወሳል።

በታሪክ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.