Fana: At a Speed of Life!

የእንጦጦ ፓርክ ለአካባቢው እናቶችና ወጣቶች የተስፋ ብርሀን ማዕከል መሆን ጀምሯል – ወይዘሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 5 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የእንጦጦ ፓርክ ለአካባቢው እናቶችና ስራ አጥተው ለቆዩ ወጣቶች የተስፋ ብርሀን ማዕከል መሆን መጀመሩን የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡
በዛሬው እለት ምክትል ከንቲባዋ በእንጦጦ ፓርክ ውስጥ የስራ እድል ከተፈጠረላቸው እናቶች እና ወጣቶች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
በከተማዋ ኢኮኖሚውን ማሳደግ እና መልካም ገጽታን በከፍተኛ ደረጃ መገንባት የሚችሉ እንጦጦን የመሰሉ ብዙ ፕሮጀክቶች አሉ ብለዋል።
ወይዘሮ አዳነች አያይዘውም ወጣቶች የተፈጠሩ የስራ እድሎችን ሳይንቁ በአግባቡ በመጠቀም በጥሩ ስነ ምግባር እና በመረዳዳት መንፈስ ሌሎችንም በሚጠቅም መንገድ መስራት አለባቸውም ነው ያሉት፡፡
የስራ እድል ተጠቃሚ የሆኑት እናቶች እና ወጣቶች ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ከአራት ወረዳዎች እና ከሱሉልታ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ወጣቶቹ እና እናቶቹ ፓርኪንግ፣ ደረቅ ቆሻሻ እና መልሶ መጠቀም የተሰማሩባቸው የስራ ዘርፎች ሲሆኑ ÷ በጠቅላላው በእነዚህ ዘርፎች 1 ሺህ ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ምክትል ከንቲባዋ አስታውቀዋል።
በእድሉ መጠቀሚያ ምዕራፍ ላይ ያሉት እናቶችም ሆኑ ወጣቶች እድሉን ለተሻለ የኑሮ ለውጥ ሊጠቀሙበት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
በትዝታ ደሳለኝ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.