Fana: At a Speed of Life!

ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ የእምቦጭ አረምን የመከላከል ዘመቻ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፡ ጥቅምት 05 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከጥቅምት 9 እስከ ህዳር 9 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ የእምቦጭ አረምን የማስወገድ ተግባር እንደሚከናወን የአማራ ክልል መንግሥት አስታወቀ፡፡
የመጀመሪያው ግብ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ጣናን ከእምቦጭ በመታደግ ወደነበረበት መመለስ መሆኑን የክልሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ገልጿል።
አሁን ላይ 4 ሺህ 300 ሄክታር የጣና ሐይቅ ክፍል በእምቦጭ የተወረረ ሲሆን፥ ዘጠኝ ወረዳዎች፣ ሦስት ዞኖች እና አንድ ከተማ አስተዳደርን እንደሚያካልልም ተመላክቷል።
ወደ አረም ማስወገድ ሥራው ሲገባም ሰው የሚንቀሳቀስበት መንገድ ከፈታ እንደሚከናወንም ታውቋል።
ሰው በቀላሉ ተንቀሳቅሶ ለመሥራት በሚያስችል መልኩ እንደሚሠራም የኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊው አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ተናግረዋል።
የክልሉ ገጠር መንገድ ባለሥልጣን የቤት ሥራ ተሰጥቶ መንገዱን እየሠራ እንደሆነም አስታውቀዋል።

የጣናን ህልውና  መታደግ  ለአማራ ክልል ብቻ የሚተው ሳይሆን ሁሉም ክልሎች  እንዲሳተፉ የፌደራል መንግስት መወሰኑን አስረድተዋል።

በአንድ ወር ለሚከናወነው የዘመቻ ሥራ በቀን ከ250 እስከ 300 ሰው በቀበሌ ደረጃ እንደሚሠማራና የሚያስተባብር የክልል እና የፌደራል አካላት የተካተቱበት ኮሚቴ እንደተቋቋመም አቶ ግዛቸው ገልጸዋል።

እምቦጭ በተከሰባቸው 30 ቀበሌዎች ሁሉም ክልሎች  ተከፋፍለው እንደሚሰሩትም ነው ዳይሬክተሩ የተናገሩት።

በናትናኤል ጥጋቡ

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.