Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከተሰናባቹ የጃፓን አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የስራ ጊዜያቸውን ካጠናቀቁት በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ዳይሱኪ ማጹናጋ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይቱ አምባሳደር ሬድዋን የጃፓኑ አምባሳደር በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግነዋል።

በቀጣይም የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰሩ እምነታቸው መሆኑንም ገልጸዋል።

አምባሳደር ዳይሱኪ ማጹናጋ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ቆይታቸው ለስራቸው መሳካት ከኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነዋል።

በቀጣይም የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት ለማጠናከርም ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.