Fana: At a Speed of Life!

በስፖርት አመራርነት የሚታወቁት አቶ ያሚ ከበደ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ ውስጥ በስፖርት አመራርነት እጅግ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው አቶ ያሚ ከበደ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡
 
አቶ ያሚ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ66 ዓመታቸው በትናንትናው ዕለት ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት፡፡
 
አቶ ያሚ ስራ ከጀመሩበት ከ1965 ዓ.ም ጀምሮ በትምህርት ሚኒስቴር በሰውነት ማጎልመሻ በመምህርነት፣ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝነት እና የቴክኒክ ዳይሬክተርነት የፌደራል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር እና በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ አገልግለዋል፡፡
 
እንዲሁም የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ እንዲሁም በተቋሙ እስከ 2005 ዓ.ም ድረስ በአማካሪነት መስራታቸው ተነግሯል፡፡
 
የአቶ ያሚ ከበደ የቀብር ስነስርዓት በዛሬው ዕለት ጉለሌ አዲሱ ገበያ በቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸም ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.