Fana: At a Speed of Life!

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ታጣቂዎች 900 እስረኞችን አስለቀቁ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቃዊ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ቤኒ ከተማ ታጣቂዎች 900 እስረኞችን ማስለቀቃቸው ተገለፀ።

ከካንግባዩ እስር ቤት ካመለጡት 900 እስረኞች መካከል የታጣቂ ቡድን አባላት እንደሚገኙበት ቢቢሲ የከተማዋን ከንቲባ ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

አሁን ላይ 110 የሚሆኑ ወንጀለኞች በእስር ቤቱ እንደሚገኙ የተነገረ ሲሆን ታጣቂዎቹ እስረኞችን ማስለቀቅ የሚያስችሉ ቁሳቁሶችን ይዘው ነበር ተብሏል።

የቤኒ ከተማ ከንቲባ ሞዴስቴ ባክዋናምሃ ለተፈጸመው ድርጊት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችን ተጠያቂ አድርገዋል።

ከእስር ቤቱ ካመለጡት በከተማዋ የተደበቁ ሊኖሩ እንደሚችሉ የተገመተ ሲሆን የከተማ ነዋሪም ድርጊቱን እንዲያወግዝ ጠይቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.