Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል ከ10 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የሚያለሙ ከፍተኛ ማሽነሪዎች ለአርሶ አደሩና በግብርና ለተሰማሩ ወጣቶች ሊከፋፈሉ  ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ከ10 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የሚያለሙ ከፍተኛ ማሽነሪዎች ለአርሶ አደሩና በማህበር ተደራጅተው በግብርና ለተሰማሩ ወጣቶች እንደሚከፋፈሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ አስታወቁ።

ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉን የግብርና ልማት ለማዘመን የክልሉ መንግሥት በቁርጠኝነት እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ እና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማን የክልሉ የመስኖ ልማት ቢሮ ለግብርና ልማት ያስመጣቸውን ማሽነሪዎች ጎብኝተዋል።

የክልሉ የመስኖ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ አብዱራህማን ኢድ ማሽነሪዎቹ በከፍተኛ ወጪ የተገዙ 102 ለግዙፍ የእርሻ ሥራ የሚውሉ የውሃ ፓምፖች፣ 150 መካከለኛ የመስኖ ሥራ የሚውሉ የውሃ ፓምፖችና 470 ትናንሽ ፓምፖች መሆናቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኃላፊው አክለውም ማሽነሪዎቹ ፍትሀዊ በሆነ መልኩ እንደሚከፋፈሉና የክፍፍሉ ስራም ከወረዳዎች ጋር በጋራ በመሆን እንደሚከናወን ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.