Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሸገር ማስዋብ ፕሮጀክትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኤርትራዉ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር በመሆን አዲስ አበባ ውስጥ በእንጦጦና አካባቢው የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ።

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ መግባታቸው የሚታወስ ነው፡፡

ፕሬዚዳንቱም በዛሬው ዕለት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር በመሆን በእንጦጦ አካባቢ የሚገኘውን የሸገር ማስዋብ ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በዚሁ በእንጦጦ አካባቢ የፕሮጀክቱ አካል ሆነው እየተካሔዱ ያሉ የመንገድና ሌሎች የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ከልኡካን ቡድናቸው ጋር በመሆን መጎብኘታቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል፡፡

እንዲሁም ፕሬዚዳንት የአንድነት ፓርክን መጎብኘታቸው የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.