Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ በስፖንጅ ፋብሪካ ውስጥ የተነሳ እሣት ንብረት አወደመ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 12 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ በስፖንጅ ፋብሪካ ውስጥ የተነሳ እሣት ከ500 ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት ማውደሙን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለፀ።

በክፍለ ከተማው ወረዳ 3 ራስ ደስታ አካባቢ በአንድ ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ባረፈ ስፖንጅ ፋብሪካ ላይ የተነሳው የእሣት አደጋ መንስኤው አልታወቀም።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ አደጋው ትናንት ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም ሌሊት መከሰቱን ለኢዜአ ገልጸዋል።

አደጋውን ለመቆጣጠር 62 የአደጋ ሠራተኞችና 12 ተሽከርካሪዎች ተሰማርተው በተደረገው ርብርብ 25 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማትረፍ እንደተቻለም ተናግረዋል።

አደጋውን ለመቆጣጠር 84 ሚሊየን ሊትር ውሃና 200 ሊትር ፎም ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን ÷ ከ500 ሺህ ብር በላይ የተገመተ ንብረት በእሣቱ ወድሟል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስና የአካባቢው ኅብረተሰብ ከእሣትና አደጋ ሠራተኞች ጋር በጋራ ባደረጉት ርብርብ እሣቱን መቆጣጠር መቻሉንም ገልፀዋል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.