Fana: At a Speed of Life!

የቱርኩ ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን በቱኒዚያ ድንገተኛ ጉብኝት አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን በቱኒዚያ ድንገተኛ ጉብኝት እያደረጉ ነው።

ፕሬዚዳንቱ በቱኒዚያ ጉብኝታቸው በጎረቤት ሊቢያ የተኩስ አቁም ማድረግ በሚቻልበት አግባብ ላይ ከፕሬዚዳንት ካይስ ሰይድ ጋር ተወያይተዋል።

ከዚህ ባለፈም ሃገራቸው ጥያቄ ከቀረበላት ወደ ሊቢያ ወታደር ለመላክ ፈቃደኛ ስለመሆኗም መሪዎቹ በጋራ በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል።

የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት አንካራ ከሊቢያ ጋር የፀጥታና ወታደራዊ ትብብርን ጨምሮ ሁለት ስምምነቶችን ከተፈራረሙ ከወር በኋላ የተደረገ ነው።

ቱርክ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እውቅና ለተሰጠውና መቀመጫውን ትሪፖሊ ላደረገው የፋይዝ አል ሳራጅ አስተዳደር እውቅና ትሰጣለች።

ፕሬዚዳንት ኤርዶኻንም የጀኔራል ከሊፋ ሃፍታር ወታደሮችን እንቅስቃሴ ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ሃገራቸው ፍላጎት እንዳላት በተደጋጋሚ ሲገልጹ ቆይተዋል።

ምንጭ፦ ሬውተርስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.