Fana: At a Speed of Life!

የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች የእንቦጭ አረም ለማጥፋት በሚደረገው ዘመቻ ላይ ለመካፈል ጣና ተገኝተዋል

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የእንቦጭ አረምን ከጣና ሐይቅ ለማስወገድ ለአንድ ወር የተላለፈውን ሀገራዊ ዘመቻን ተከትሎ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጣና ተገኝተዋል።

በዘመቻው ከሚኒስትሯ በተጨማሪ ከህዝብ ተወካዮች የከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽንና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አመራርና አባላት፣ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር፣ የትራንስፖርት ዘርፍ ተጠሪ ተቋማት ዳይሬክተሮች እና የሁሉም ክልልና ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ዘርፍ የሥራ ኃላፊዎች በዘመቻ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ሚኒስትሯ ሀገር አቀፍ የንቅናቄ ዘመቻ በተያዘለት ጊዜ ግቡን እንዲመታ በቁርጠኝነት እና ጠንካራ ተነሳሽነት እየተሳተፈ ያለውን አርሶ አደሩን፣ የአካባቢው ማኅበረሰብ እንዲሁም የፌደራልና የክልል አመራር አካላትን አመስግነዋል።

ህዳሴ ግድብ ያለ አባይ: አባይ ያለ ጣና አይታሰቡምና በህብር ጣናን ከእምቦጭ እናድን የሚለውን ጥሪ በመቀበል ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪያቸውን ማቅረባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.