Fana: At a Speed of Life!

የቅድመ ስኳር ምልክት በሚታይበት ጊዜ የማይመከሩ ምግቦች

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ቅድመ የስኳር በሰውነት ውስጥ ያለው የስኳር መጠን መሆን ከሚገባው ከፍ ሲል ግን ደግሞ የስኳር በሽታ የሚባል ደረጃ ላይ ያልደረሰ ለበሽታው የመጋለጥ ምልክት ነው።

የህክምና ባለሙያዎችም ቅድመ ስኳርን ለመከላከል የአኗኗር ዘይቤን እና አመጋገብን ማስተካከል እንደሚገባ ይመክራሉ።

ከዚህ አንጻር አንድ ሰው የቅድመ ስኳር ምልክት በታየበት ጊዜ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ምግቦች ባይመገብ ይመረጣል፤

. የፍራፍሬ ጭማቂ

የፍራፍሬ ጭማቂ የበዛ ስኳርና የያዘና በጥሬው ከሚመገቡት ፍራፍሬ በበለጠ ጣፋጭ በመሆኑ በቅድመ ስኳር ምልክት ወቅት መመገቡ ለስኳር በሽታ የመጋለጥ እድልን ስሚያሰፋ አይመከርም።

.አልኮል መጠጥ

የአልኮል መጠጦች በውስጣቸው ያለው የስኳር መጠን ቢለያይም የስኳር በሽታ ታጋላጭነትን ያሰፋሉ።

አልኮል የሚጠጡ ሰዎች አንድም በደማቸው ውስጥ ያለው የስኳር መጠን በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል አልያም በተቃራኒው ይወርዳል።

ይህ ደግሞ የቅድመ ስኳር ምልክት ለታየባቸው ሰዎች እጅጉን አደገኛ መሆኑን ባለሙያዎች ይመክራሉ።

ለዚህም አልኮልን ማስወገድ አልያም የስኳር መጠናቸው አነስተኛ የሆኑ እንደ ወይን ያሉ የአልኮል መጠጦችን በውሃ በመበረዝ መጠቀም።

.ቅባት የዛባቸው ምግቦች

ቅባት የበዛባቸው ምግቦች የኢንሱሊንን ስራ በማስተጓጎል የስኳር በሽታ ተጋላጭነትን ሊጨምሩ ይችላሉ።

.ጣፋጭ (ስኳር የበዛባቸው) ምግቦች

ስኳር ለሰውነታችን አስፈላጊ ቢሆንም በብዛት መውሰድ ግን ለስኳር ህመም ተጋላጭ ስለሚያደርገን በቅድመ ስኳር ህመም ወቅት ማስወገድ ይገባናል።

ጣፋጭ ምግቦችን መመገብ ካስፈለገም ከተዘጋጁ በኋላ ሳይሆን በጥሬው (በፍራፍሬ) መልክ ቢመገቡ ከጣፋጭ ምግቦች ማግኘት የሚገባዎትን በቂ የስኳር መጠን ያገኛሉ።

ባለሙያዎቹ ጣፋጭ ምግቦችን አለመመገብ ሳይሆን መመጠኑን ይመክራሉ።

.ሩዝ፣ ነጭ ዱቄትና ዳቦ

ሌላው እና በቅድመ የስኳር ወቅት መዘውተር የሌለበት ምግብ ደግሞ ሩዝ እና ከስንዴ የሚዘጋጅ ነጭ ስንዴና ዳቦዎችን ነው።

እንደ ባለሙያዎቹ ገለጻ ነጭ ዱቄት በፋብሪካ በሚመረትበት ወቅት በሚኖረው የማቀነባበር ሂደት ለሰውነት አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ያጣል።

በዚህ ሂደት የሚቀረው ነገር የስኳር መጠኑ ብቻ በመሆኑም የቅድመ ስኳር ምልክት በሚታይ ጊዜ መጠቀሙ አደጋ እንዳለው ይገልጻሉ።

ምንጭ፡-http://hhdresearch.org/

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.