Fana: At a Speed of Life!

የእናቶችና ሕጻናት ጤና አገልግሎት ሀገር አቀፍ የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 17 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ2012 በጀት ዓመት የእናቶችና ሕጻናት ጤና አገልግሎት ሀገር አቀፍ የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በአዳማ ከተማ ተካሂዷል።

የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማው የፌደራል ጤና ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎችና የክልል ጤና ቢሮ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው የተጀመረው።

የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ÷ ሀገራዊ የግምገማ መድረኩን በከፈቱበት ወቅት እንደተናገሩት በኮቪድ 19 ወረርሽኝን ምክንያት በእናቶችና ህፃናት ጤና ላይ ተጨማሪ ስጋቶች መጋረጡ ለእናቶችና ህፃናት የሚሰጡ የጤና አገልግሎቶች ፈተና እንዲገጥማቸው አድርጓል።

በወርሽኙ ወቅት በአፋጣኝ የተወሰዱ እርምጃዎች በተለይም ችግሩን በጊዜ የመታደግ ስራ በመሰራቱ ሊከሰት የሚችለውን ፈተና እና አደጋ በመቀነስ ተገቢውን ስራ ለመስራት መቻሉን ሁሉንም ባለድርሻ አካል የሚያስመሰግን ነው ብለዋል።

በጤና ሚኒስቴር የእናቶች ህጻናት ጤና እና ስርዓተ ምግብ ዳይሬክተር ዶክተር መሰረት ዘላለም በበኩላቸው ÷ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆየው የግምገማ መድረክ በእናቶች ህፃናትና በስርዓት ምግብ ዳይሬክቶሬት ስር ያሉትን ስራዎች ለመገምገም እንደሚያግዝ ጠቅሰዋል።

ከዚህ ባለፈም በቀጣይ በተሻለ መልኩ ውጤት ለማስመዝገብና የእናቶችንና ህፃናትን ሀገራዊ የጤና ጥያቄ ለመመለስ የሚረዳ መድረክ መሆኑንም ጠቁመዋል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.